EthiopiaNews

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር 1 ቢሊዮን የቡና ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተደረገ።

በሀገሪቱ በሚገኙ በሁሉም ቡና አብቃይ አካባቢዎች አንድ ቢሊዮን የቡና ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር  ታጋይ ኑሩ ተናግረዋል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ከዚህ በፊት የተተከሉ የቡና ችግኞች ከ90 በመቶ በላይ መጽደቃቸው የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሩ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ቡና አምራች ባልሆኑ አካባቢዎች ጭምር ቡናን በማስፋት የቡና ምርታማነት እንዲጨመር የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ቡናን ወደተለያዩ ሀገራት በመላክ ከፍተኛ ገቢ የምታገኝ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከቡና ወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ታቅዶ ባለፉት ወራት 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ማግኘት መቻሉ ተገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews