በዛሬው ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ የኢራን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ በፊት ወደነበረበት ዋጋ መመለሱ ተነግሯል፡፡
በዛሬው ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ የኢራን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ በፊት ወደነበረበት ዋጋ መመለሱ ተነግሯል፡፡
ላለፉት አራት ወራት ያህል ዋጋው አልቀመስ ብሎ የነበረው የዓለም የነዳጅ ዋጋ አሜሪካና ኢራን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን እና የሆርሙዝ ሰርጥ መከፈትን ተከትሎ ከፍተኛ ቅናሽ ማሳየቱ ነው የተሰማው፡፡
የዓለም የነዳጅ ዋጋ መለኪያ የሆነው ብሬንት ክሩድ በበርሜል ከዚህ በፊት ሲሸጥበት ከነበረው እስከ 130 ዶላር ዋጋ አሁን ላይ እጅግ በመቀነስ የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 72 ዶላር እየተሸጠ ነው ተብሏል፡፡
ለዋጋ መቀነሱ ዋንኛው ምክንያት የሆርሙዝ ሰርጥ መከፍትን ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ለዓለም ገበያ መቅረብ በመጀመሩ ነው የሚለው ዘ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ይህ ዋጋ ከዚህ በታችም ሊቀንስ ይችላል ብሏል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
