በያዝነው ዓመት እንዲካሄድ ቀጠሮ የተያዘለትን የኢትዮጵያ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫን በግንቦት መጨረሻና ሰኔ ወር መጀመሪያ ለማካሄድ መታሰቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ ከሲቪል ማህበራትና ከሚዲያ አካላት ጋር በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዋና ዋና ተግባራት፣ የምርጫ ሰሌዳ በተመለከተና የኮቪድ 19 የጥንቃቄ እርምጃዎች ላይ ውይይት እያካሄደ ነው::

በውይይቱ ላይም አጠቃላይ ጊዜያዊ የምርጫ ሰሌዳን በተመለከተ ነው በተጠቀሱት ጊዜያት ምርጫውን ለማድረግ መታሰቡን ያሳወቀው፡፡

ከዚህ ባሻገር ቦርዱ ለምርጫው የጥንቃቄ መመሪያዎችን አውጥቶ እንደሚንቀሳቀስ ያሳወቀ ሲሆን ለዚህም ተጨማሪ የ1.1 ቢሊዮን ብር በጀት መጠየቁን የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ጠቅሰዋል፡፡#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs