InternationalNews

በፍቅረኛዋ በግፍ የተገደለችው አትሌት!

ኡጋንዳዊቷ የማራቶን ሯጭ ርብቃ ቼፕቴጌ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ በፍቅረኛዋ በደረሰባት ጥቃት ህይወቷ አለፈ፡፡

በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ የተሳተፈችው የ33 አመቷ ኡጋንዳዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ ርብቃ ቼፕቴጌ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ከፍቅረኛዋ ጋር በተፈጠረ የመሬት ውዝግብ ምክንያት ፍቅረኛዋ ዲክሰን ኒዲማ አንድ ጄሪካን ቤንዚን በሰውነቷ ላይ በማርከፍከፍ እንድትቃጠል በማድረግ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡
አትሌቷ ከአንድ ወር በፊት በተካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ 44ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቋን አስታውሶ የዘገበው አሶሼትድ ፕሬስ ነው፡፡