ባልደራስ የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የምርጫ መመዘኛ ደረጃዎችን ያላሟላ ነበር ብሏል፡፡
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በቅድመ ምርጫ ሂደት ላይ አደረግኩት ያለውን ጥናት ተከትሎ ከቀናት በፊት የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የምርጫ መመዘኛ ደረጃዎችን ያላሟላ ነበር ብሏል፡፡ የምርጫ ሂደቱ የተበላሸ መሆኑ ውጤቱም ሊበላሽ እንደሚችል ማሳያ ነው ያለው ፓርቲው በምርጫው ላይ የተሳተፍኩት በኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን የበኩሌን ለመወጣት መሆኑ ይታወቅልኝ ሲል ለአዲስ ነገር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ የታጀበ ነው ባለው ምርጫ የተከሰቱ ችግሮችን በጥልቀት እየመረመርኩ እገኛለሁ ያለ ሲሆን እስካሁን ደረሼበታለሁ ባለው ሁኔታም ምርጫው ነፃ፣ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ አልነበረም የሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርሱ ተግባራት መኖራቸውን ገልጿል፡፡ በዚህም በድምፅ አሰጣጥ ወቅት ግንዛቤ ለመስጠት የተሰየሙት የምርጫ አስፈፃሚዎች የገዢው ፓርቲ እንዲመረጥ የሚረዳ ገለጻ ሲያካሂዱ ነበር ያለው ፓርቲው በመራጮች ምዝገባ ወቅት ያልነበሩ አዳዲስ ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎችን ከመክፈት በተጨማሪ የማይታወቁ የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው በድምፅ