EthiopiaNews

ብልጽግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ማሸነፉ ይፋ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ በሥራ አመራር ቦርዱ የተረጋገጡና የፀደቁ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶችን የምርጫ ውጤቶችን ትላትና ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ብልፅግና ፓርቲ  ከ501 የፓርላማው ወንበር 438ቱን መቀመጫዎች ሲያሸንፍ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ኢዜማ 13 የፓርላማ ወንበሮች፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን 6 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮችን አሸንፏል።

የፓርላማ ወንበሮችን ያገኙ የግል ተወዳዳሪዎችም መኖራቸው በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ ግብር ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv