EthiopiaNews

“ቦይንግ ዘግይቶብኛል”

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ እንዲሰራለት ያዘዛቸው አውሮፕላኖች በመዘግየታቸው አየር መንገዱ አውሮፕላኖችን ለመከራየት እንደተገደደ ገልጿል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ለብሎምበርግ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ካለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በእጁ መግባት የነበረባቸው 737 ማክስ የመንገደኞች አውሮፕላኖችና 777 ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች እስካሁን አልደረሱም ብለዋል።

በታሪኩ አስቸጋሪ ቀውስ ገጥሞታል የሚባለው ቦይንግ በበርካታ አየር መንገዶችም የመዘግየት ቅሬታ እየቀረበበት ይገኛል።