ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ለኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ነገ ለሚከበረው የ1442ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ፕሬዝደንቱ ሰለአረፋ በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ዘርዘር ያለ መልዕክት ያስተላላፉ ሲሆን በዓሉን እንደዚህ ቀደሙ ሁሌ በመተሳሳብ እና በሰላም ማሳለፍ እንደሚገባም ገልጸዋል። በተጨማሪም የኮቪድ ፕሮቶኮልን በመጠበቅ ከጥንቃቄ ጋር ማሳለፍ ይኖርብናልም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢኤስ አዲስ ነገር