‘ትሪዮጵያ ” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ ተባለ።

በቅርብ በተቋቋመው 1888 EC በተባለ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ስቱዲዮ ”ትሪዮጵያ ” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ ተባለ። መተግበርያው በቱሪዝም መላክ ለጎብኚዎች አስፈላጊ መረጃ በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል። የ1888EC መስራች የሆነው አቶ ሰለሞን ካሳ ለቴክኖሎጂ አፍላቂዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና በድህነትና ኋላቀርነት ላይ አዲሱን ትውልድ ለማዝመት ስቱዲዮው መቋቋሙን በመክፍቻው ስነስርአትላይ ተናግሯል። አቶ ሰለሞን ካሣ በኢቢኤስ ቴሌቭዥን ላለፉት በርካታ አመታት “ቴክ ቶክ ዊዝ ሰለሞን ” የተሰኘውን የቴክኖሎጂ ፕሮግራም በማዘጋጀት ይታወቃል።