ትራምፕ ስለኢራን
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት በሚለው ውሳኔ መስማማታቸውን ገለፁ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቻይና ያደረጉትን የ2 ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚያ ቀደም ብለው በሰጡት ቃለ መጠይቅ የቻይናው ፕሬዝዳንት ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዲኖራት ሊፈቀድላት አይገባም በሚለው ውሳኔ ተስማምተዋል ብለዋል፡፡
ትራምፕ አክለውም ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መክፈት እንዳለባት ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ መናገራቸውን ጠቅሰው ሌሎች የሀገራቸው መሪዎች ሊፈቱት ያልቻሉትን በርካታ ችግሮች በሁለት ቀናት የቻይና ጉብኝት መፍታት መቻላቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ስለነበራቸው ንግግር ያሉት ነገር ባይኖርም የቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ቤጂንግ በኢራን ጦርነት መሰላቸቷን ገልጿል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
