ቻይና ከአንደኛው የባህር ሰርጓጅ መርከቧ የቦለስቲክ ሚሳኤል የተኩስ ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች።
የቻይና ባለስልጣናት እንዳሉት ሚሳኤሉ ላይ የተገጠመው እውነተኛው የፈንጂ አረር ሳይሆን በተመሳሳይ ክብደትና ቅርፅ የተሰራ ቁስ ነው።
ቻይና ሙከራው የተለመደ የዓመታዊ ወታደራዊ ልምምዴ አካል ነው ብትልም አውስትራሊያ ግን ሙከራውን ፀብ አጫሪ ድርጊት ስትል አውግዛለች።
ቻይና ሙከራውን ያደረገችውም አውስትራሊያ ከጐረቤቷ ፊጂ ጋር የወታደራዊ ትብብር ስምምነትን ከተፈራረመች በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
ቻይና ከዚህ ቀደም ከትንሽቱ የደሴት አጋር ሰለሞን አይላንድስ ጋር ግንኙነት ለማጠናከር ከተስማማች በኋላ አውስትራሊያም ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰደች ትገኛለች።
የአሁኑ የቻይና የሚሳኤል ሙከራ ከመደረጉ በፊት ቻይና ለአውስትራሊያ ብታሳውቅም አውስትራሊያ ግን ድርጊቱን በቀላሉ አላየውም እያለች ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
