EthiopiaNews

አሁንም ከባድ ዝናብ ይኖራል ተባለ

በሚቀጥሉት 10 ቀናት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ሱዳን እና በመዕራብ ኤርትራ የተወሰኑ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ እንደሚኖር የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አስታውቋል።

በቅርቡ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እና በሱዳን በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የበርካቶች ህይወት ሲያልፍ ሌሎች ደግሞ በጉዳቱ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚኖረው ከባድ ዝናብ የመሬት መሰንጠቅ፣ የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቡ አይዘነጋም።