EBS SPORT – አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ የመልሱን ጨዋታ እንደ አዲስ እንደሚጫወቱ ተናግረዋል

የኢትዮጵያ ከ 17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ዋና አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ የመልሱን ጨዋታ እንደ አዲስ እንደሚጫወቱ ተናግረዋል
ቡድኑ በመጀመሪያ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ተጉዞ ከሜዳው ውጪ የ 3 ለ0 ድል ይዞ መመለሱ የሚታወቅ ሲሆን የመልሱን ጨዋታም በመጭው እሁድ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የሚከውን ይሆናል ይህንን ተከትሎ አሰልጣኙ ከ ኢቤኤስ ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ ለጨዋታው በጥሩ ሁኔታ እየተዘጋጁ እንድመኢገኙና በመልሱ ጨዋታ ከሜዳቸው ውጭ ያስመዘገቡትን ውጤት በመርሳት በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት ለፊት የሚያደርጉትን ጨዋታ ለማሸነፍ እንደሚጥሩ ተናግረዋል ቡድኑ ከልምምድ በተጨማሪ አቋሙን ለመፈተሽ ሁለት የወዳጅነት ጨውታዎችን ማድረጉ ይታወቃል በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ከ 17 አመት በታች አለም ዋንጫ ለማለፍ በማጣሪያው እየተካፈሉ የሚገኙት ታዳጊዎቹ በመልሱ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካን በድምር ውጤት አሸንፈው የሚያልፉ ከሆነ በመጨረሻው ማጣርያ ከናይጄሪያ እና ግብጽ አሸናፊ ጋር የሚፋጠጡ ይሆናል