Sports

EBS SPORT- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ይደረጋሉ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ይደረጋሉ
በነገው እለት ጅማሮውን በሚያደረገው የ21ኛ ሳምንት ጨዋታም ባህርዳር ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር በ9፡00 ሰዓት እንዲሁም በተጠባቂው ጨዋታ መከላከያ ከ ኢትዮጵያ ቡና በ 12 ሰዓት ይገናኛሉ በርካታ ደጋፊዎች ከየአቅጣጫው ወደ ከተማዋ በመጓዝ ድጋፋቸውን የገለጹበትና የደመቀ ትዕይንት የታየበት የአዳማ ቆይታ በ 21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚጠናቀቅ ሲሆን ከ ሳምንት እረፍት በኋላም ተረኛዋ አዘጋጅ ባህርዳር ከተማ ከ 22ኛ ሳምንት ጀምሮ ያሉትን ጨዋታዎች ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠበቅ ላይ ትገኛለች ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬደዋ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታን በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታድየም የሚደረግ የመጀመሪያ ጨዋታ መሆኑን ይታወቃል ከአዳማ ከተማ በፊት ሃዋሳ ከተማ እና ድሬደዋ ከተማ የ2014 የውድድር አመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ማሰናዳታቸውም ይታወሳል
እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ 44 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሊጉን በ 10 ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኝ ሲሆን በውድድር አመቱ ወጥ አቋም እያሳየ የማይገኘው የአምናው ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ በ 34 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል በዘንድሮው የውድድር አመት ተጠናክረው የቀረቡት ሃዋሳ ከተማና ወላይታ ዲቻ በአጼዎቹ በጎል ክፍያ ተበልጠው 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል በሊጉ ግርጌ የሚገኙት ጅማ አባጅፋርና ሰበታ ከተማ 13 ነጥቦችን ብቻ መሰብሰብ ችለዋል