EthiopiaNews

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ይቅርታ ጠየቀ

የኢቢኤስ ስፖርት ዝግጅት ክፍል ከአሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ጋር በስልክ ቆይታ አድርጓል።

አሰልጣኙ የተደረገልን ሽልማት አሁንም በቂ ነው ብዬ አላምንም ይሄ ደግሞ የኔ ብቻ ሳይሆን የበርካታ አሰልጣኞች እምነትም ነው ያለ ሲሆን ሆኖም በቤተ መንግስት በተደረገው የሽልማት መርሃግብር ላይ ላሳየሁት ስሜታዊነት የተሞላበት ምላሽ  ሁሉንም ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ ሲል ለዝግጅት ክፍላችን ተናግሯል።

የአትሌት ታምራት ቶላና ትዕግስት አሰፋ አሰልጣኝ የሆነው ገመዶ ደደፎ የሁለት ሚሊየን ብር ሽልማት በትላንትናው እለት ቢበረከትለትም እኔ ወርቅ ፣ ብር እና ዲፕሎማ አስገኝቼ ሁለት ሚሊዮን ብር ብቻ መሸለሜን እንደ ስድብ እቆጥረዋለሁ በማለት ሽልማቱን አልቀበልም ማለቱ ይታወሳል፡፡