አቢሲኒያ ባንክ
ባንኩ በፈረንጆቹ 2022/23 ሒሳብ ዓመት 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።
አቢሲኒያ የተጠናቀቀውን የሒሳብ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባከናወነው 27ኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጉባዔ ላይ እንደተናገረው የተገኘው ገቢ ካለፈው ሒሳብ ዓመት የ12 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አሳውቋል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ 22 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መድረሱ የተጠቀሰ ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ ሀብትም 189 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል፡፡
በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት የተገኘው የውጭ ምንዛሬ መጠን 457 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሆኑን ያሳወቀው ባንኩ ይህም ከባለፈው ሒሳብ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
በበጀት ዓመቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚም ከፍተኛ ችግር ተጋርጦበት ነበር ያለው ባንኩ የሰላምና ጸጥታ ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ የምግብ ዋስትና ማጣትና የድርቅ አደጋ ተዳምረው ኢኮኖሚውን መፈተናቸውን አመላክቷል፡፡
ለኤቢኤስ ዘገባ -ዘነበ ሃይሉ
::