EthiopiaNews

አንጋፋው ደራሲና ኢንጂነር ታደለ ብጡል ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የ2008 ዓ.ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የነበሩት ኢንጅነር ታደለ ብጡል የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ በትላንትናው እለት በ97 አመት የልደት ቀናቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።

የባንክ ባለሙያ፣ ኢንጅነርና ደራሲ የነበሩት ታደለ ብጡል የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ፣የሐኪም ወርቅነህ እሸቴ፣ የአፄ ቴዎድሮስን እና የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስን ግለ ታሪክ ጽፈዋል። ከዚህ ባሻገር ማራዧት እና ሶስትዮሽ የተሰኙ የግጥም መድብሎችንም አበርክተዋል።

ጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መፅናናትን ይመኛል።