አዲስ ነገር – ምናባዊው አገልግሎት

ከህግ እውቅና ውጪ ክሪፕቶ ከረንሲና ቢትኮይንን የመሳሰሉ የምናባዊ የንብረትና የገንዘብ ወይም የቨርቹዋል እሴት አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
ይህ ተግባር ከብሄራዊ ባንክ እውቅና ውጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበትና በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ መሆኑን ባንኩ ጠቁሟል፡፡
ምናባዊ ንብረትንና ገንዘብን ለግብይት ወይም ለክፍያ የመጠቀም ሂደት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅና ያልተሠጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባር እራሱን እንዲቆጥብ ባንኩ አሳስቧል።
በተጨማሪ ባንኩ ይህን ተግባር በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህግዊ እርምጃ እንደሚወስድ ለአዲስ ነገር በላከው መግለጫው ጠቁሟል፡፡
ህብረተሰቡም ይህን ህገወጥ ተግባር የሚሰሩ አካላት ሲመለከት ይጠቁመኝ ሲል የኢትዮያ ብሄራዊ ባንክ ጥሪ አቅርቧል ፡፡
የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ይደነግጋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New