News

አዲስ ነገር – የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ

የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የድጎማ ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚገልፅ መለያ ይፋ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እንዳለው መለያው ሁለት አይነት መሆኑንና ለመደበኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎችና በክልል ለሚገኙ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግል ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የድጎማው ተጠቃሚ መሆናቸውን ለነዳጅ ማደያዎችና ለሚመለከታቸው ሌሎች አካላት መረጃ የሚሠጥ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በዚህም ሙሉ ሰማያዊ ቀለም ያለው መለያ ለሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የሚያገለግል ሲሆን በነጭ መደብ የተዘጋጀው መለያ ደግሞ በክልል ለሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎ ሰጪ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግል መሆኑን ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New