News

አዲስ ነገር – የኢንፎርሜሽን ሶሳይቲ

በፈረንጆቹ 2022 ህዳር ወር በአዲስ አበባ ሊካሄድ በተዘጋጀው የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ሀገራት እንዲሳተፉ ኢትዮጵያ መጠየቋ ተነገረ፡፡
ይህ የተነገረው ከግንቦት 30 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2022 በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ኢንተርናሽናል የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት በተደረገበት ወቅት ሲሆን በአለም ዓቀፉ የኢንፎርሜሽን ሶሳይቲ ፎረም ላይ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ከዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታና ንግድ አንፃር በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና የዲጂታል ንግድን ለማቀላጠፍ የሚረዱ መሰረታዊ ስራዎችን ማለትም በፖሊሲና አስቻይ የህግ ማዕቀፎች፣ በአይሲቲ መሰረተ ልማት ዘርፍ፣ በዲጂታል ክህሎት እና በኢኖቬሽን ዘርፍ በመሰራት ላይ ያሉትን ሀገራዊ ስራዎችና ጥረቶችም የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያ በህዳር ወር በአዲስ አበባ ለምታስተናግደው የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ሁሉም ሀገራት እንዲሳተፉ ጥሪ መቅረቡንም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል ።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New