News

አዲስ ነገር – የቀጣዩ የ2015 በጀት

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀትን 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ሆኖ እንዲጸድቅ ውሳኔ አሳለፈ።

በጀቱ ከ2014 ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የ111 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር ወይም የ16 ነጥብ 59 በመቶ ጭማሪ ያለው ሲሆን የበጀት ዝግጅቱ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን ከማስፈጸም አኳያ የሀገር ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳትና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።

እንዲሁም የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎችን ለማሳካት ማዕከል ያደረገ ሲሆን ለ2015 በጀት ዓመት ለመደበኛ ወጪ 347 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 218 ነጥብ 11 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ለክልል መንግሥታት ድጋፍ 209 ነጥብ 38 ቢሊዮን ብርና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ደግሞ 12 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዟል ነው የተባለው።

አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በስፋት ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወስኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New