አዲስ ነገር – በግለሰቦች ደረጃ የሚካሄድ የንግድ ስራ ፈጠራ ውድድር ሊደረግ ነው

በሀገሪቱ ያሉ የንግድ ሀሳቦችን ለማፍለቅና ስራ ፈጣሪነትን ለማበረታታ በማሰብ በግለሰቦች ደረጃ የሚካሄው የስራ ፈጠራ ውድድር ሊከናወን ስለመሆኑ ተሰምቷል።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጀዋለሁ ያለው ይህ ውድድር በሀገሪቱ ስራ ፈጣሪነት ከማበረታታት ባለፈ በኢኮኖሚው ዘርፍ የራሱ አሻራ ማኖር የሚችሉ የንግድ ሀሳቦች በሁለት ዙር ለውድድር እንደሚቀርቡ ነው የተገለፀው።
በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር ምርጥ 10 የንግድ ሀሳቦች የሚመረጡ ሲሆን በሁለተኛው ዙርም ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የስራ ማስጀመሪያ ካፒታል እንደሚመቻች ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
ስለሆነም የራሴ የንግድ ሀሳብ አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፌስቡክ ገጽ ላይ በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት አጭር ቪድዮ በመላክ በውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላል የተባለ ሲሆን ለውድድሩ የሚቀርቡ ሀሳቦችም በኢትዮጵያ የሚተገበሩና የስራ ባለቤትነታቸው የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተገልጿል። መረጃውን ያገኘነው ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው ፡፡