አዲስ ነገር – አይ ኤም ኤፍ ለጋና የ3 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ብድር አፀደቀ።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ለጋና የ3 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ብድር አፀደቀ።
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና በተለይ የኮሮና ወረርሽኝ በምጣኔ ሃብቷ ላይ ያደረሰውን ጉዳት እንድትቋቋም የሚያግዛትን የ 3 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለጋና ማጽደቁን የገለጹት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጃዪቫ ናቸው።
የባንኩ አዲሱ ብድር በቀውስ ውስጥ የነበረውን የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ወደ መረጋጋት እንዲገባ ከፍተኛ አተዋፅኦ ያደርጋል መባሉን ዩ.ፒ.አይ ዘግቧል፡፡
🇸🇩#ሱዳን
የመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን በሱዳን ከወር በላይ በቀጠለው ጦርነት ከ 1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል አለ፡፡
የኮሚሽኑ ቃለ አቀባይ ማቲው ሳልትማርሽ በሱዳኑ ግጭት 843 ሺ የሚሆኑ ዜጐች በአገር ውስጥ ሲፈናቀሉ የተቀሩት ሩብ ሚሊዮን ሰዎች ከሱዳን ወደ ሌሎች ሀገራት ተሰደዋል ነው ያሉት፡፡
ከተሰደዱት የሱዳን ዜጎች መካከል 110 ሺ የሚሆኑት ወደ ግብፅ መሰደዳቸው ተነግሯል፡፡
ዘገባው የሬውተርስ ነው፡፡

🇸🇾#ሶሪያ
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አልአሳድ ከ12 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአረብ ሊግ ሀገራት ጉባኤ እየታደሙ መሆኑ ተነገረ ።
ፕሬዚዳንት በሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የአረብ ሊግ ጉባኤ እየታደሙ መሆኑን የገለጸው የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ነው፡፡
የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈይሰል ቢን ፋርሃን የፕሬዝዳንት አልአሳድ በጉባዔው መታደም “የአረብ ሀገራት ከመናቆር ወጥተን ወደ ትብብር የገባንበት ምሳሌ ማሳያ ነው፤” ሲሉ የጉብኝቱን ታሪካዊነት አስረድተዋል።
የአረብ ሊግ ጉባኤ የሶሪያው ፕሬዚዳንት አልአሳድ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መፍቀዱን ተከትሎ አሜሪካ ተቃውሞ ማሰማቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
🇯🇵#ጃፓን
በጃፓን ሂሮሺማ ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ያሉት የቡድን 7 ሀገራት መሪዎች በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንዲጣል ተስማሙ።
ሀገራቱ በስምምነታቸው መሰረት ሩሲያ ከየትኛውም የቡድን 7 ሀገራት ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ምርቶችን እንዳታገኝ ጥብቅ ቁጥጥር እናደርጋለን ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
መሪዎቹ በሩሲያ ተወራለች ላሏት ዩክሬን የልማት ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በጃፓን ሂሮሺማ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው በዚሁ ጉባኤ ለመታደም ወደ ጃፓን ማቅናታቸው ተሰምቷል፡፡
በጉባዔው የበለጸጉት ሀገራት መሪዎች ተጽዕኖዋ እየጨመረ በመጣው የቻይና ጉዳይ ላይም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New