News

አዲስ ነገር – ጆ ባይደን የቡድን 7 ሀገራት ጉባዔን ለመታደም ጃፓን ሂሮሺማ ገቡ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቡድን 7 ሀገራት ጉባዔን ለመታደም ጃፓን ሂሮሺማ ገቡ።
ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ጉባኤ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ አዲስ ማዕቀብ እንዲጣል ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ግፊቱ ያስፈለገው በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች በመጣል ዙሪያ በቡድኑ መሪዎች ልዩነት ስላለ ነው ተብሏል፡፡
መሪዎቹ በአየር ንብረት ለውጥ ፣ በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ እና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡


ዓለም አቀፉ የረድኤት ድርጅት ኦክስፋም የቡድን 7 ሀገራት ለአዳጊ ሀገራት መክፈል የሚጠበቅባቸውን የ13 ትሪሊየን ዶላር በአስቸኳይ ክፍያ መፈጸም እንዲጀምሩ ጠየቀ።
ኦክስፋም የቡድን 7 ሀገራት በተለያየ ጊዜ አዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን እንዲቋቋሙ እንከፍላለን ሲሉ ቃል የገቡትን የ13 ትሪሊየን ዶላር ገንዘብ መክፈል እንዲጀምሩ ነው አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ ያሳሳበው ።
ሀገራቱ ከአዳጊ እና ሌሎች ሀገራት ከብድር እና ወለድ ክፍያ ጋር በተያያዘ በየቀኑ የሚሰበስቡትን 232 ሚሊየን ዶላር እንዲያቆሙ እና ገንዘቡ በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ለሚኖሩ ህዝቦች ልማት እንዲውል ኦክስፋም ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የበለፀጉት አገራት ከአውሮፓውያኑ 2020 እስከ 2025 ድረስ ለሀገራቱ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ በየአመቱ 1 መቶ ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ቢገቡም ይሄንንም አልፈፀሙም ሲል ኦክስፋም ወቅሷል።
በበለፀጉት የቡድን 7 ሀገራት ሚሊየነሮች እና ቢሊየነሮች ላይ እስከ 5 በመቶ ግብር ቢጣል ለአዳጊ አገራት ልማት የሚውል በየአመቱ 9 መቶ ቢሊዮን ዶላር ማሰባሰብ እንደሚቻል በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።
🇷🇺#ሩሲያ
የምግብ ሰብሎች ከዩክሬን ወደቦች ወደ ተለያዩ ሀገራት እንዲከፋፈሉ የተደረሰው ዓለም አቀፍ ስምምነት ለ 2 ወራት መራዘሙ ተሰማ፡፡
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የሩሲያ መንግስት እህል ከዩክሬን ወደቦች እንዲወጣ ፈቃደኝቱን መግለፁን ተከትሎ ስምምነቱ ለ60 ቀናት መራዘሙን ይፋ አድርገዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በቱርክ አስተባባሪነት ተደርሶ የነበረው ይኸው ስምምነት ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት እየቀሩት ነው የሩሲያ መንግስት ለቀጣይ ሁለት ወራት እንዲራዘም መስማማቱ የተነገው፡፡
ሩሲያ ምግብ እና የማዳበሪያ ግብአቶችን በምዕራባዊያኑ ማዕቀብ ሳቢያ መላክ አልቻልኩም በሚል በተደጋጋሚ ለስምምነቱ መራዘም ይሁንታ አልሰጥም ማለቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
🇺🇦#ዩክሬን
ዩክሬን በሩሲያ ከተተኮሱባት 30 ሚሳኤሎች ዉስጥ 29ኙን አከሸፍኩ አለች ።
ይሁንና በኦዴሳ ከተማ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው መገደሉን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች መጎዳታቸው ተነግሯል።
ሩሲያ በወር ውስጥ ብቻ ለ9 ኛ ጊዜ የዩክሬንን መዲና ኪየቭን በሚሳኤል እየደበደበች መሆኗን ኤፒ ዘግቧል ።
ዩክሬን የመልሶ ማጥቃቷን አጠናክራ እንድትቀጥል ምዕራባዊያኑ አገራት ዘመን አፈራሽ የጦር መሳሪያዎችን ለመስጠት ቃል እየገቡ መሆኑ ነው፡፡

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New