አዲስ ነገር – ኤ.አይ የደረሰበት ፈጣን የእድገት ደረጃ ለሰው ልጆች አስጊ መሆኑን የመስኩ ምሁራን ገለፁ፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም በምህጻረ ቃሉ “ኤ.አይ” የደረሰበት ፈጣን የእድገት ደረጃ ለሰው ልጆች አስጊ መሆኑን የመስኩ ምሁራን ገለፁ፡፡
የኦፕን ኤ አይ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማንን ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎች “ኤ.አይ ” ልክ እንደ “ወረርሽኝ እና የኒውክለር የጦር መሣሪያ” ሁሉ በአስጊነቱ ትኩረት ሊያገኝ ይገባል ሲሉ ሞግተዋል፡፡
የኤ አይ የጡት አባት የሚባሉት ጆፍሬይ ሂንተን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ “እጅግ አደገኛ ነው፤” ሲሉ ከወራት በፊት በብርቱ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም ።
ይሁንና አንዳንድ ባለሙያዎች ኤአይ ያን ያህል ስጋት አደደለም ሲሉ መግለፃቸውን ቢቢሲ በዘገባው ዳሶታል፡፡
🇸🇩#ሱዳን
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የተደረሰውን የተኩስ አቁም ለማራዘም መስማማታቸውን አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ አደነቁ፡፡
ሁለቱ አሸማጋይ ሀገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ የሱዳን ተፈላሚ ወገኖች ለ 5 ቀናት የተኩስ አቁሙን ለማራዘም መወሰናቸው “የሚደነቅ ተግባር ነው፤” ብለውታል፡፡
አሸማጋዮቹ እንደሚሉት ምንም እንኳን በወጉ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ባይከበርም ይብዛም ይነስም ለሁለት ሚሊዮን ሕዝብ ድጋፍ ለማቅረብ አስችሏል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በበኩሉ የሱዳን ውጊያ ከጀመረ ከ6 ሳምንታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለካርቱም ነዋሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ መጀመሩ ነው በዘገባው የተብራራው።
🇷🇺#ሩሲያ
ሩሲያ በመዲናዋ ሞስኮ በሰው አልባ አውሮፕላን የተቃጣውን ጥቃት ዩክሬን ናት የፈጸመችው ስትል ከሰሰች።
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ድርጊቱ የሩሲያን ሕዝብ ለማስደንገጥ የተደረገ ነው ብለውታል፡፡
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የድሮን ጥቃቱ የዩክሬን የሽብር ተግባር ነው ሲል ኪየቭን ወንጅሏል።
በሞስኮ ዛሬ ተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በርካታ ህንፃዎች መጐዳታቸውን ነው የሩሲያ ባለስልጣናት ይፋ ያደረጉት ።
ይሁንና የዩክሬን መንግስት በክሬምሊን የቀረበበትን ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ሲል ማጣጣሉን ቢቢሲ ዘግቧል ።
🇨🇳#ቻይና
የቻይና እና የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች የጋራ ጉባኤ እንዲያካሂዱ በአሜሪካ የቀረበውን ጥሪ ቻይና ውድቅ አደረገች ።
“በሲንጋፖር የቻይና እና የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች ውይይት እንዲያደርጉ ለቻይና ያቀረብነውን ግብዣ የቤጂንግ ባለስልጣናት ውድቅ ማድረጋቸውን በደብዳቤ ምላሽ ሰጥተውናል፤” ብሏል የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው ።
የመከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃለ አቀባይ ፓትሪክ ራይደር ሁለቱ ኃያላን ሀገራት ወደ ግጭት እንዳያመሩ ድርድር አስፈላጊ ነው ማለታቸውን አናዶሉ ዘግቧል ።
በደቡብ ምሥራቅ እስያ ለሁለቱ ሀገራት መካከል ላለው ውጥረት መንስኤ የሆኑት የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ በቀጣናው ሁለቱም ሀገራት የተጽዕኖ አድማሳቸውን ለማስፋት የሚያደርጉት ጥረት፣ በቻይና በኩል የሚቀነቀን የድንበር ይገባኛል ጥያቄና የታይዋን ጉዳይ መሆናቸውን ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡
የቻይና የመከላከያ ሚስቴር ባለስልጣናት ከዚህ ቀደምም ከአሜሪካ አቻቸው ጋር እንደማይወያዩ መግለጻቸውን ነው የአናዶሉ ዘገባ ያስታወሰው፡፡
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New