አዲስ ነገር – ካምላ ሃሪስ በሶስት የአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተነገረ ።

🇺🇸#አሜሪካ
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካምላ ሃሪስ በሶስት የአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተነገረ ።
ምክትል ፕሬዚዳንት ካምላ ሀሪስ የአሜሪካ-አፍሪካ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝታቸውን በአውሮፓውያኑ ማርች 26 በጋና በመጀመር በቀጣይ በታንዛኒያ እና ዛምቢያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተዘግቧል።
የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ካምላ ሃሪስ በአፍሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት የአሜሪካ እና የአፍሪካ አገራትን በዴሞክራሲ እና በኢኮኖሚ ይበልጥ ትስስር እንዲፈጥሩ ያደርጋል መባሉ ተሰምቷል፡፡
ከአውሮፓውያኑ 2023 ወዲህ አፍሪካን ከጐበኙ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት 18ኛዋ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካምላ ሃሪስ እንደሚሆኑ የዘገበው ዘ ኢስት አፍሪካን ነው።

🇷🇺#ሩሲያ
ሩሲያ ከዩክሬን ወደቦች እህል እንዲወጣ የተደረሰውን ዓለም አቀፍ ስምምነት በ60 ቀናት እንዲራዘም ውሳኔ አሳለፈች።
በመንግስታቱ ድርጅት እና ቱርክ በፈረንጆቹ 2022 እህል ከዩክሬን ወደቦች እንዲወጣ የተደረሰው ስምምነት ከመጠናቀቁ 4 ቀናት አስቀድሞ ነው የሩስያ ባለስልጣናት ስምምነቱን ለቀጣዮቹ 60 ቀናት ያራዘሙት ።
የዩክሬን የመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሩሲያ ስምምነቱን ቢያንስ ለ120 ቀናት ልታራዝም ይገባ ነበር ሲል ቅሬታ ማቅረቡን ፍራንስ 24 ዘግቧል ።
🇨🇳#ቻይና
ቻይና ለውጭ ሃገራት ጎብኝዎች ለ3 አመታት የቆለፈችውን ድንበሯን ልትከፍት መሆኑ ተሰምቷል።
ቻይና የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሚል ከዚህ ቀደም ወደ አገሪቱ በሚገቡ የውጭ አገራት ጐብኚዎች ላይ የጣለችውን ጥብቅ ክልከላ በማንሳት ድንበሯን ክፍት ልታደርግ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡አሁን ላይ ድንበሯን ክፍት ያደረገችው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በሚገባ መቆጣጠር በመቻሏ መሆኑ ነው የተገለፀው ።
የቪዛ እገዳው መነሳቱን ተከትሎ በኮሮና የተጐዳው የሃገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ መልሶ ሊያንሰራራ እንደሚችል ፍራንስ 24 ዘግቧል።
🇲🇼#ማላዊ
ማላዊ እና ሞዛምቢክን ለሁለተኛ ጊዜ በመታው “የፍሬዲ” አውሎ ነፋስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 100 በላይ መድረሱ ተዘገበ ።
ከአመታት ወዲህ እጅግ አደገኛ በተባለው በፍሬዲ አውሎ ነፋስ በተመቱት ሞዛምቢክ እና ማላዊ አገራት ለህልፈት ከተዳረጉት ከ100 ሰዎች በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልተለዩ በርካታ ሰዎች የደረሱበት አይታወቅም ተብሏል።
በሞዛምቢክ እና ማላዊ በደረሰው በዚሁ የአውሎ ነፋስ አደጋ በርካታ መኖሪያ ቤቶች ፣ ህንጻዎች ሁሉ መውደማቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል።
የፍሬዲ አውሎ ነፋስ ክፉኛ በመታት ማላዊ ብቻ 99 ሰዎች መሞታቸውን እና በሞዛምቢክ እና ማላዊ በአንድ ወር ዉስጥ ብቻ በሁለት ዙር በደረሰው የአውሎነፋሱ አደጋ 136 ዜጐች መሞታቸው ተዘግቧል።

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New