News

አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

🇨🇳#ቻይና
ቻይና ከሩስያ እና ኢራን ጋር በመተባበር የተቀናጀና ግዙፍ ነው ያለችውን የባሕር ኃይል የጦር ልምምድ ይፋ አደረገች ።
የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር “ሴኩሪቲ ቦንድ 2023” የተባለውን የባሕር ኃይል የጦር ልምምድ ከሩስያ እና ኢራን ጋር በኦማን ባሕረ ሰላጤ ለ4 ቀናት እንደሚያካሂድ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ።
የቤጂንግ ባለሥልጣናት የባሕር ኃይል ልምምዱ ቻይና ከሩሲያ እና ኢራን ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር የሚያጠናክር እና በቀጣናው አገራት መተማመንን የሚፈጥር ነው ብለዋል ።
የዛሬ ወር ቻይና ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሩሲያ የተሳካ ነው የተባለውን የባሕር ኃይል ልምምድ ማድረጋቸውን አርቲ ዘግቧል ።
🇸🇦#ሳዑዲ አረቢያ
ሳዑዲ አረቢያ ከኢራን ጋር የሰላም ስምምነት መድረሷን ተከትሎ በኢራን ግዙፍ ኢንቨስትመንት ልታካሂድ ማቀዷን አስታወቀች።
የሳዑዲ አረቢያ የገንዘብ ሚኒስትር መሐመድ አልጃን የሰላም ስምምነት ከቴህራን ጋር መደረጉ “አበረታች” መሆኑን ገልፀው በኢራን መጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንት ለማድረግ አቅደናል ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ በኢራን የምናደርገው ኢንቨስትመንት ለቴህራን በጣም ጠቃሚ ሲሆን በቀጣናው ዘላቂ መረጋጋት እና ሰላምን ያመጣል ሲሉ መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል ።
ኢራን የሳዑዲ አረቢያ ጐረቤት አገር በመሆኗ የተደረሰውን የሰላም ስምምነቱን ትሩፋቶች ወደ ኢንቨስትመንት እድሎች ልንቀይረው ይገባል ሲሉ የሳዑዲ አረቢያው የገንዘብ ሚኒስትር መግለፃቸው በዘገባው ተመልክቷል ።
🇮🇹#ጣሊያን
ባለፉት 3 ወራት ዉስጥ ብቻ ከአፍሪካ የተነሱ ከ20 ሺ የሚበልጡ ህገወጥ ስደተኞች ወደ ጣሊያን መግባታቸውን የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ።
የጣሊያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የ3 ወራቱ አሃዝ ከአምናው ተመሳሳይ ሩብ ዓመት አንፃር በአራት እጥፍ ጭማሪ ያሳየ ነው ብሏል በመግለጫው።
ሩሲያ በሳህል አገራት የምታካሂደው የወታደራዊ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ ወደ ጣሊያን የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር እንዲጨምር ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው ሲል የጣሊያን መንግስት ማስታወቁን አናዶሉ ዘግቧል ።
የሮም መንግስት የህገወጥ ስደተኞችን ለመግታት በሚል የጣሊያን የድንበር አካባቢዎችን በቴክኖሎጂ የማጠናከር ሥራ እያካሄደ መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል ።
🇺🇸#አሜሪካ
ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያው ፌስቡክ ባለቤቱ ሜታ ኩባንያ ለሁለተኛ ጊዜ 10ሺ ሰራተኞቹን ከሥራ ማሰናበቱን ይፋ አደረገ፡፡
የሜታ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ከዚህ ቀደም ውጤታማ እና አትራፊ ሆነን ለመቀጠል ባወጣነው ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት 10ሺ የሜታ ኩባንያ ሰራተኞችን ከሥራ አሰናብተናል ብለዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዙከርበርግ ኩባንያቸው ሜታ በሜታቨርስ ቴክኖሎጂ ላይ በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች እያፈሰሰ መሆኑን ነው ያስታወቁት፡፡
የሜታ ኩባንያ በአውሮፓውያኑ 2022 መጨረሻ ከአጠቃላይ የድርጅቱ ሰራተኞች 13 ከመቶውን ወይም 11ሺ የሚሆኑ ሰራተኞችን ከሥራ ማሰናበቱን ኤፒ በዘገባው ተመልክቶታል።

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New