አዲስ ነገር – ዋትስአፕ አዲስ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መጠበቂያ ዘዴ

ዋትስአፕ አዲስ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መጠበቂያ ዘዴ ይፋ አደረገተጠቃሚዎች በቡድን ከሚደረጉ ምልልሶች ሳያሳውቁ መውጣት፣ግላዊ መረጃዎችን መቆጣጠር (online status) እና መልዕክቶች ላይ ያሉ ምስሎችን መገደብ (block screenshots on view once messages) ይችላሉ ተብሏል።የግዙፉ ኩባንያ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ የዋትስአፕ አዲሱ ገጽታ ፊት ለፊት የመነጋገር ያህል ግላዊነቱ የተጠበቀ ነው ሲል ገልጾታል።ይህ የዋትስአፕ አዲስ ገጽታ በዩናይትድ ኪንግደም ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ የማስተዋወቅ ዘመቻ የሚደረግ ይሆናልም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New