አዲስ ነገር – ዓለም

🇺🇦#ዩክሬን የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ላደረሰችው ግዙፍ ውድመት ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ።ፕሬዝዳንቱ ለክሬምሊን አሰተዳደር የካሳ ክፍያ ጥያቄ ያቀረቡት ከሩሲያ ጋር የሚካሄድ የሰላም ድርድር በተመለከተ ቅድመ ሁኔታዎችን ይፋ ባደረጉበት ጊዜ ነው ። ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከካሳው በተጨማሪ ሩሲያ የመንግስታቱ ድርጅት ያወጣውን ቻርተርም እንድታከብር እንጠይቃለን ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

#የመንግስታቱ ድርጅት የመንግስታቱ ድርጅት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን በመለየት ለአገራት ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ የ3 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ፕሮጀክቱ በቀጣዮቹ 5 አመታት የሚተገበር እንደሚሆን አስታውቀዋል።አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ፕሮጀክቱ ሁሉንም የአለም አገራት ከአየር ንብረት ለውጥ ጥፋት የሚታደግ እንደሆነ መናገራቸውን የፈረንሳዩ ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ዘግቧል።

🇲🇼#ማላዊ የአለም የጤና ድርጅት በማላዊ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የሚረዳ 2.9 ሚሊዮን ብልቃጥ የኮሌራ ክትባት ለአገሪቱ አስረከበ።የማላዊ የጤና ሚኒስቴር ክትባቱን መረከቡን ገልፆ በቀጣይ ሳምንታት ሁለተኛውን ዙር የኮሌራ ክትባት ዘመቻ እንደሚያካሄድ ነው ያስታወቀው።በማላዊ ባለፉት 7 ወራት ውስጥ በቀጠለው በዚሁ የኮሌራ ወረርሽኝ 200 ሰዎች ሞተው ወደ 7ሺህ የሚጠጉ በበሽታው መያዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።🇬🇧

#ብሪታንያ በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ሰራሽ መንገድ የበለፀገ ደም ለሁለት ሰዎች መሰጠቱ ተሰምቷል።በብሪታንያ የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪው ኘሮፌሰር አሽሌይ ቶዬ በቤተ ሙከራ የተመረተውን ሰው ሰራሽ የቀይ የደም ሴል የተሰጣቸው ሁለት ሰዎች አንዳች የጐንዮሽ ምልክት አለማሳየታቸው በህክምና ፈጠራው ተስፋ እንድንሰንቅ አድርጓል ብለዋል።የብሪታንያ ሳይንቲስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቁት ይኸው የሰው ሰራሽ ደም ልዩ ልዩ በሽታዎችን በሚገባ ለማከም እንደሚረዳ ጂየሩሳሌም ፖስት ዘግቧል ።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New