Others

አዲስ ነገር – የዓለም ውሎ

🇪🇬ግብፅ በግብፅ በተከፈተው የመንግስታቱ ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ላይ ከ 100 በላይ የአገራት መሪዎች ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።በግብጿ የመዝናኛ ከተማ ሻርምኤልሼክ የ50 አገራት መሪዎች የመክፈቻ ስነ ስርአቱ ላይ መታደማቸው ሲነገር የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዬ ጉቴሬዝ የተደቀነብንን የጥፋት አደጋ መቀልበስ የምንችለው ስንተባበር ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ይሁንና በዚሁ የመንግስታቱ ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ላይ የቻይና እና የህንድ አገራት የልኡካን ቡድን በጉባኤው አለመታደማቸውን ኤፒ ዘግቧል።

🇺🇸የአሜሪካ ምርጫበነገው እለት ለሚካሄደው የአሜሪካ የግማሽ አመት የም /ቤት ምርጫ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የቀድሞው መሪ ዶናልድ ትራምፕ የመጨረሻ ቀን የምረጡኝ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ ።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በኒውዮርክ ከተማ ባደረጉት የምረጡኝ ዘመቻ የአሁኑ የም /ቤት ምርጫ የአሜሪካ ቀጣይ 20 አመታት እጣ ፈንታን የሚወስን በመሆኑ የዲሞክራት ፓርቲ እጩዎችን ምረጡ ሲሉ ቀስቅሰዋል ::በሌላ በኩል የአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኦሃዬ ግዛት ተገኝተው ዴሞክራቶች ከተመረጡ ሀያሏን አሜሪካ እንደ ኩባ እና ቬንዙዌላ ያደርጓታል ሲሉ መወረፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል

🇮🇹ጣሊያንአዲሷ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ስደተኞችን አስመልክቶ እያራመዱት ያለዉ ፖሊሲ ተቃውሞ ገጥሞታል።ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ባሕር አቋርጠው ወደ ጣሊያን የሚያቀኑ ስደተኞችን ለመታደግ በወደብ አካባቢዎች ያሉ በርካታ የነፍስ አድን የረድኤት ድርጅቶች አገልግሎት እንዳይሰጡ አዲስ ባወጡት ፖሊሲ አግደዋል።በዚህም ቢያንስ 200 ስደተኞች የከፋ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ነው አርቲ የዘገበው ።

🇺🇸አሜሪካየአሜሪካ ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያዎች ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ብቻ 200 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘታቸው ተነግሯል።በመካሄድ ላይ ያለዉ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ነው ግዙፎቹ የአሜሪካ ኩባንያዎች በ6 ወራት ውስጥ ብቻ 200 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኙት።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሁን ኩባንያዎቹ ያስገቡት ቢሊዮን ዶላሮች የነፋስ አመጣሽ ትርፍ የጦርነት ውጤት ነው ሲሉ መውቀሳቸውን አርቲ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New