አዲስ ነገር – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር

7ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የተማሪዎችና የመምህራን የፈጠራ ውድድር አውደ ርእይ በቀጣይ 3 ቀናት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕዩ በከተማ ደረጃ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ ከሰኔ 9 እስከ 11/2014 ዓ.ም ድረስ “የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ፥ የብልጽግና ጉዛችንን በሳይንስና ፈጠራ ዕውን እናደርጋለን” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ በወዳጅነት አደባባይ እንደሚከበር ቢሮው ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ያስታወቀ ሲሆን ውድድሩ በዋናነት በሳይንስ ፈጠራ የዳበረ ጤናማ ውድድርን ለመፍጠር ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግሯል።

በፈጠራ አውደ ርዕዩም ከአዲስ አባባ በ11ዱ ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡና ከሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች እንደየ ክፍል ደረጃቸው በተለያዩ ዘርፎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን በማቅረብ እንደሚወዳደሩ ሰምተናል፡፡

እንዲሁም በውድድር መርሃግብሩ በሳይንስና ሒሳብ ትምህርቶች፣ በአይ ሲቲ፣ በልዩ ፍላጎት እንዲሁም በስነ ጥበብ ዘርፎች በተማሪዎችና በመምህራን የፈጠራ ስራዎች የሚቀርቡ ሲሆን በተመረጡ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ተዳኝተው የተሻሉ ፈጠራዎች ለሽልማት ይበቃሉ ተብሏል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New