Sports

EBS SPORT – እለታዊ መረጃዎች

  • ጥሩ እንጫወታለን ብዬ ባስብም በዚህ አይነት ብልጫ ግብፅን እናሸንፋለን ብዬ አልጠበኩም ሲሉ የኢትዮጵያ ብ/ዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናግረዋል ። በሳምንቱ መጀመሪያ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኙ በመጀመሪያው 45 ከግብፅ ጋር  ያሳየነውን አቋም ወደፊት በሙሉ 90 ደቂቃ ማሳየት እንደምንችል አምናለሁ ሲሉ በቡድኑ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡
  • በ18ኛው የኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የሚወክሉ እጩ አትሌቶች ይፋ ሆነዋል፡፡ ከ ጁላይ 15-24 በሚደረገው የአለም የአትሌቲክስ ድግስ ላይ ኢትዮጵያ ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን በወንዶች እና ሴቶች ተካፋይ የምትሆን ሲሆን 38 ተሳታፊ እና ተጠባባቂ አትሌቶችን የኢት  ፌዴሬሽን በሳምንቱ መጀመሪያ ይፋ አድርጓል፡፡ 
  • የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን ኮንትራት ለማራዘም የተጀመረ ምንም አይነት ድርድር እንደሌለ ተገለፀ፡፡ በመጪው መስከረም የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውል መጠናቀቅን ተከትሎ ጥያቄ የቀረበላቸው የፌዴሬሽኑ የፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን አሁን እናንተ ስታነሱት ነው ደንገጥ ያልኩት እስካሁን ውላቸውን ለማራዘም የተጀመር ድርድር የለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
  • የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የፊታችን ረቡዕ በባህርዳር አለም አቀፍ ስቴዲየም መደረጋቸውን ይቀጥላሉ፡፡ በዚህም ጠዋት 4 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ ይጫወታል፡፡ 7 ሰዓት ላይ ደግሞ የወላይታ ድቻ እና አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ ይጀመራል፡፡ የእለቱ የመዝጊያ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማን በ10 ሰዓት ያገናኛል፡፡
  • በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በድል ለተመለሰው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የእውቅና እና የገንዘብ ሽልማት ሊበረከትለት ነው፡፡  14 ሜዳልያዎችን በማግኘት በውደድሩ 5ኛ ደረጃን ያገኘው ቡድኑ የፊታችን ረቡዕ ወደ ሀገሩ የሚገባ ሲሆን የአቀባበል እና የማበረታቻ ሽልማት ከፌዴሬሽኑ እንደሚበረከትለት ተገልፅዋል፡፡
  • ሊቨርፑል ኡራጋዊውን የቤኒፍካ አጥቁ ዳርዊን ኑኔዝን በ85 ሚሊየን ፓውንድ የግሉ ማድረጉ ተረጋግጧል፡፡ 41 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦች ያስቆጠረው ኑኔዝ በመርሲሳይዱ ክለብ እስከ 2028 የሚያቆየው የስድስት አመት ኮንትራት እንደሚፈራም የተሰማ ሲሆን በክለቡም የምንግዜውም ውዱ ተጫዋች ይሆናል፡፡
  • በማንችስተር ዩናይትድ አርሰናል እና ቶትንሃም ሆትስፐርስ የዝውውር እቅድ ውስጥ ይገኝ የነበረው ፓብሎ ዲባላም ወደ ኢንተር ሚላን ለማምራት ሁሉን ነገር ማጠናቀቁን ከጣሊያን የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡  የ28 አመቱ ሁለገብ አጥቂ በኔራዙሪዎቹ ቤት የ3 አመት ውል እንደሚፈርም የሚጠበቅ ሲሆን አመታዊ የ6 ሚሊየን ዩሮ ደሞዝ ተከፋይም ይሆናል፡፡
  • የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ክለብ ቼልሲ ኦስማን ደምበሌን ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ለማምጣት መቃረቡ ተገለፀ፡፡  ከባርሴሎና ጋር ኮንትራቱን ያጠናቀቀው ፈረንሳዊው የመስመር ተጫዋች ከቀድሞ አሰልጣኙ ቶማስ ቱሄል ጋር መስራትን ምርጫው ማድረጉን ተከትሎ ወደ ቼልሲ ለመምጣት በመርህ ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል፡፡
  • ቶትንሃም ሆትስፐርስ ይቬስ ቤሱማን ከብራይተን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ የ25 አመቱ ማሊያዊ አማካይ በያዝነው በሊጉ ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱን ተከትሎ የበርካታ ክለቦች አይን  ቢያርፍበትም የሰሜን ለንደኑ ክለብ በ25 ሚሊየን ፓውንድ ተጫዋቹን ለማዛወር ከብራይተን ጋር መስማማቱ ተገልፅዋል፡፡
  • 31ኛውን የአለም ዋንጫ ተሳታፊ ሀገር ለመለየት በተደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የኦሺኒያዋ አውስትራሊያ ፔሩን በመለያ ምት 5-4 በማሸነፍ ወደ ኳታሩ የአለም ዋንጫ ማቅናቷን አረጋግጣለች፡፡ በዚህም አውስትራሊያ በመጪው ህዳር በሚጀመረው የአለም የእግር ኳስ ድግስ በምድብ 4 ከፈረንሳይ ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ጋር የምትገናኝ ይሆናል፡፡
  • የአውሮፓ ሀገራት ሊግ የምድብ ማጣሪያ በመጨረሻ ሳምንት 4ኛ ጨዋታዎች ፈረንሳይ ሽንፈት ስታስተናድግ ዴንማርክ ድል ቀንቷታል፡፡ በአውሮፓ ሀገራት ሊግ ውድድር ማሸነፍ የተሳናት  ፈረንሳይ በሜዳዋ ስታድ ደፍራንስ በክሮሺያ 1-0 ተሸንፋለች፡፡ ምድቧን  በ9 ነጥቦች እየመራች ያለችው ዴንማርክ ኦስትሪያን 2-0 ረታለች፡፡  

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New