አዲስ ነገር – የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት እንጦጦ ተራራ ላይ በሚገኘው የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ የምርምር ማእከልን ለማስፋፋት በተሰጠው 16 ሄክታር መሬት ላይ የገብስ ሰብል ዘርተዋል።
ተቋሙ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ቦታውን የተረከበው ኢትዮጵያ በቀጣይ በስፔስ ዘርፍ ለምታከናውናቸው ፕርጅርክቶች ግንባታ ይውል ዘንድ ታስቦ ቢሆንም ስራው እስኪጀመር ድረስ መሬቱ አገልግሎት እንዲሰጥ በማሰብ ሰብሉን መዝራቱን ገልጾልናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የምርት መጠንን አስቀድሞ በመተንበይ የሚያስችል መተግበሪያን ለመሞከር ታሳቢ በማድረግ ጭምር ቦታውን ለእርሻ ለማዋል እንዳስፈለገው ኢንስቲቲዩቱ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም በትላንትናው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ምክንያት በማድረግ የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በስፍራው የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New