News

አዲስ ነገር – የዳሽን ባንክ የመረጃ ማዕከል

ዳሽን ባንክ በሀገራችን የግል የፋይናንስ ዘርፍ የመጀመሪያ ነው ያለውን የመረጃ ማዕከል በዛሬው እለት አስመርቋል።
ባንኩ 230 ሚሊየን ብር ወጪ አደርጌበታለው ያለው ቲር ስሪ የተባለውና የሰለጠነው አለም የሚመራበት የመረጃ ደህንነት ሶፍትዌር የተገጠመለት የመረጃ ማዕከል ከፍተኛ አቅም ያላቸው 1ሺህ የሚጠጉ ሰርቨሮችን የመያዝ አቅም ያለው መሆኑም ተገልጿል።
ዓመቱን ሙሉ ያለምንም መቆራረጥ ያገለግላል የተባለው ይህ የመረጃ ማዕከል እስከ 10 ዓመት የማገልገል አቅም ያለው እንደሆነና አጠቃላይ ማዕከሉ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ስራን ያቃልላል ተብሏል።
ከዚህም ባለፈ ሌሎች የፋይንናንስ ተቋማትም አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ባንኩ ይሄን የዳታ ማዕከል ገንብቶ ወደ ስራ ለማስገባት ከሀሳብ ጀምሮ አጠቃላይ 1 ዓመት ጊዜ ወስዶብኛል ያለ ሲሆን ማዕከሉን በራሱ ባለሞያዎች ለመቆጣጠርም ሰራተኞቹን ከሀገር ውጪ ልኮ እያሰለጠነ መሆኑን ተናግሯል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ሁሉም በሀገሪቱ የሚገኙ ባንኮች ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ በማዋል የህዝቡን ሀብት መጠበቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New