News

አዲስ ነገር – የኢትዮ ሱዳን ድንበር ግጭት

መንግስት በኢትዮ ሱዳን ድንበር ላይ በሱዳን ወታደሮችና የአካባቢ ሚሊሻዎች ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘኑን አስታወቀ፡፡
በህዝብ እንደራሴዎች በአሸባሪነት በተፈረጀው የህወሃት ቡድን ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ እና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መካከል የተከሰተውን ሁነት የኢትዮጵያ መንግስት መገንዘቡን አመልክቷል፡፡
ድርጊቱ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የተፈጸመው በህወሓት ቡድን የሚደገፈው የሱዳን መደበኛ ጦር ሰራዊት የኢትዮጵያን መሬት ከወረረ በኋላ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ጦር እና በአካባቢው ባለው ሚሊሻ መካከል በተፈጠረ ግጭት በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኑን በመግለጽ በቅርቡም በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ አስገንዝቧል፡፡
የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት ፀብ ጫሪ ድርጊት የፈፀመው የሱዳን ጦር ነው የሚለው መግለጫው በሁኔታው ኢትዮጵያን ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞከርን የትኛውንም ድርጊት መንግስት እንደማይቀበል ያስታወቀ ሲሆን የሱዳን መንግስት ሁነቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች በመቆጠብ የተፈጠረውን ድርጊት ሊያረግቡ የሚችሉ እርምጃዎችን እንደሚወስድ የኢትዮጵያ መንግስት ተስፋ እንደሚያደርግም መግለጫው አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም የተፈጸመው ድርጊት በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ስር የሰደደ ግንኙነት ለማፍረስ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን የገለጸው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉ ማናቸውንም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው አስገንዝቧል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New