News

አዲስ ነገር – የሰላም ተደራዳሪ ቡድን

ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እልባት ለማበጀት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙ ተገልጿል፡፡
በዚህም መሠረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የቡድኑ ሰብሳቢ መሆናቸው ሲነገር የፍትህ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቲዎስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህም በቡድኑ በአባልነት ተካተዋል ተብሏል፡፡
እንዲሁም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፣ ሌፍተናንት ጄኔራል ብርሀኑ በቀለና ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር በተመሳሳይ የቡድኑ አባል መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍትህ ሚኒስትሩና የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ትላንት አመሻሹን በሰጡት መግለጫ ፓርቲያቸው የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት ለመቋጨት የሚከተለው የሰላም አማራጭ 3 ጉዳዮችን መሰረት ያደርጋል ብለው ነበር፡፡
እነዚህም ሕገ መንግሥታዊና ሕጋዊነትን የሚያስከብር፣ የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅና በሀገር ውስጥ መፍታት ካልተቻለ በአፍሪካ ሕብረት ጉዳዩ መታየት አለበት የሚሉት መሆናቸውን መጠቆማቸው ይታወሳል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New