አዲስ ነገር – የቻይናው የመከላከያ ሚኒስትር የቻይና እና የአሜሪካ ጦርነት ዓለም አይታው የማታውቀው የከፋ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ።
የቻይናው የመከላከያ ሚኒስትር ሊ ሻንፍፉ የቻይና እና የአሜሪካ ጦርነት ዓለም አይታው የማታውቀው የከፋ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ።
የመከላከያ ሚኒስትሩ በሲንጋፖር በተካሄደ የሀገራት የፀጥታ ጉባኤ ላይ ነው ይህንን የተናገሩት፡ ፡ አክለውም ጥቂት ሀገራት በእስያ ወታደራዊ ፍጥጫን ለማባባስ እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ኃያላኑ አሜሪካ እና ቻይና ልዩነቶቻቸውን በውይይት ሊፈቱ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ይሁንና በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው የቻይናው የመከላከያ ሚኒስትር ሊ ሻንግፉ ከአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ኦስቲን ሎይድ የቀረበላቸውን የእንወያይ ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።
🇸🇩#ሱዳን
በሱዳን ተባብሶ የቀጠለውን ጦርነት ተከትሎ በጤና ተቋማት የመብራት ኃይል በመቋረጡ የጤና ባለሙያዎች የሞባይል ስልካቸውን መብራት በመጠቀም እያዋለዱ መሆኑ ተሰማ፡፡
በሱዳን ካርቱም ባለ አንድ የጤና ተቋም የሚሰሩት ዶ/ር ሆዋይዳ አህመድ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሚሰሩበት ሆስፒታል የመብራት አገልግሎት ባለመኖሩ የደረሱ እናቶችን በቀዶ ጥገና የሚያዋልዱት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የባትሪ ብርሃን ታግዘው ነው፡፡
ዶ/ር ሆዋይዳ እንዳሉት በሱዳን ውጊያው ተባብሶ በመቀጠሉ ሳቢያ በካርቱም ያሉ ሆስፒታሎች እጅግ የከፋ ችግር ውስጥ ገብተዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን 219ሺ ነፍሰ ጡር እናቶች አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላል ሲል ከወራት በፊት ማስጠንቀቁ በዘገባው ተመላክቷል፡፡
🇮🇱#እስራኤል
የመንግስታቱ ድርጅት ባለፉት 6 ወራት በእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ 112 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን አስታወቀ።
የተመድ የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) ባወጣው መረጃ ከሞቱት ፍልስጤማውያን በተጨማሪ 4ሺ 209 የሚሆኑ ለጉዳት ተዳርገዋል ብሏል፡፡
በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት አብዛኞቹ ፍልስጤማውያን በምስራቅ ኢየሩሳሌም እና እስራኤል በኃይል በያዘችው የዌስት ባንክ የሚኖሩ እንደነበር ቲ አር ቲ ዘግቧል ።
የእስራኤል የፀጥታ ሃይሎች በዌስት ባንክ እና በምስራቅ ኢየሩሳሌም 575 የፍልስጤም መኖሪያ ቤቶችን እንዳፈረሱ ተመድ ማስታወቁን ነው ዘገባው አክሎ ያስረዳው፡፡
🇸🇦#ሳዑዲ አረቢያ
ሳዑዲ አረቢያ በመጪው ሐምሌ ወር ዕለታዊ የነዳጅ ዘይት ምርት መጠኗን በ 1 ሚሊዮን በርሜል እንደምትቀንስ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ጭማሬ ማሳየቱ ተገለፀ።
የሳዑዲ ዕቅድ በእስያ ሀገራት የነዳጅ ዘይት ዋጋ በ 2 ነጥብ 4 ከመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተዘገበው።
ከነዳጅ አምራች እና ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) ጋር የሚሰሩት ኦፔክ ፕላስ የተባሉት ነዳጅ ላኪ ሀገራት ሚኒስትሮች የነዳጅ ዘይት ምርታቸውን ለመቀነስ መስማማታቸው ነው የተነገረው
የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት የነዳጅ ዋጋ እንዲዋዥቅ በማድረግ የነዳጅ አምራች እና ላኪ ሀገራትን መጉዳቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New