አዲስ ነገር – የነዳጅ ዋጋ

በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንዲቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የአለም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በየወሩ በመጨመር ላይ ቢገኝም የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባትና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል የቤንዚን የናፍጣና የኬሮሲን ወይም ነጭ ጋዝ የችርቻሮ መሸጫ በግንቦት ወር 2014 ሲሸጡ በነበሩበት እንዲቀጥሉ መወሰኑ ተገልጿል፡፡
ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን በመጠቆም በአለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማሻሻያ ሊደረግ እንደሚችልም ከሚኒስቴሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክተናል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New