Sports

EBS SPORT – ቀጣይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ እና ሌሎች መረጃዎች

👉🏾 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጭው እሁድ ወሳኙን ጨዋታ ከማላዊ ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ  ማጣርያ በምድብ አራት ከማላዊ፣ግብጽ እና  ጊኒ ጋር የተደለደለው ዋልያው የመጀመሪያ የማጣርያ ጨዋታውን የፊታችን እሁድ ከማላዊ አቻው ጋር ያደርጋል

👉🏾 የአዲስ አበባ ከተማው  ግብ ጠባቂ ዳንኤል ተሾመ  ለብሄራዊ ቡድን እመረጣለሁ ብሎ ጠብቆ እንደነበር ከ ሀትሪክ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል

የቀድሞው የአዳማ ከተማ ግብ ጠባቂ ምንም እንኳን ቡድኑ ውጤታማ ባይሆንም በግሉ ጥሩ የሚባል የውድድር አመትን እያሳለፈ ይገኛል ቡድኑን ከመውረድ ለመታደግ የቡድኑ ተነሳሽነት ምን ይመስላል በሚል ለተነሳለት ጥያቄም ቸጨዋቾችም ሆኑ አሰልጣኙ የታሪክ ተወቃሽ ላለመሆን እየጣሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል

👉🏾 ፖል  ፖግባ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እንደማይቀጥል ክለቡ አሳውቋል

በ 2016/17 የውድድር አመት ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ የተመለሰው ተጨዋቹ በቀያዮቹ ሴጣኖች ቤት የኢሮፓ ሊግና የካራባኦ ካፕ ዋንጫን አሳክቷል ፖግባ በተደጋጋሚ በኦልድትራፎርድ ክለብ  እንደማይቀጥል ሲናገር መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን  ክለቡም ተጨዋቹ በሰኔ መጨረሻ ማንችስተርን እንደሚለቅ ማረጋገጫ ሰቷል ከሱ በተጨማሪ የክለቡ አካዳሚ ፍሬ የሆነው ጄሴ ሊንጋርድም ከቀያዮቹ ሴጣኖች ጋር በይፉ ተለያይቷል

👉🏾 አርጀንቲና ጣልያንን በማሸነፍ  የፍይናሊስማ ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችሏል

የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊና  ከኮፓ አሜሪካ አሸናፊ ባገናኘው በዚህ ጨዋታ አርጀንቲና በላውታሮ ማርትኔዝ በአንሄል ዲማሪያና በፓውሎ ዲባላ ጎሎች  ጣሊያንን 3-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች ይህ የፍፃሜ ጨዋታ ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው በፈረንጆቹ 1993 ነበር

👉🏾 የኮሚኒቲ ሺልድ የፍጻሜ  ጨዋታ በኪንግ ፓወር ስታድየም እንደሚደረግ ተገልጿል

የፕርምየር ሊጉን አሸናፊ ማንችስተር ሲቲን ከ ኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊው ሊቨርፑል  ጋር  የሚያገናኘው የዘንድሮው የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ  አስቀድሞ በዌምብሌ ስታድየም እንዲረግ መርሃ ግብር ቢወጣለትም ስታድየሙ የ2022 የሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የሚካሄድበት መሆኑን ተከትሎ ጨዋታው በሌስተር ሲቲ ስታድየም እንዲካሄድ መደረጉ ተገልጿል

👉🏾 የፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጨዋቾች  ማህበር የአመቱን ምርጥ ተጨዋች እጩዎች ይፉ አድርጓል

ቨርጅል ቫን ዳይክ ፣ ሀሪ ኬን ፣ ሳዲዮ ማኔ ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሞሀመድ ሳላህ እና ኬቨን ዴ ብሩይን በእጩ ዝርዝር ውስጥ ሲካተቱ ፊል ፎደን ፣ ኮነር ጋላገር ፣ሬሲ ጀምስ ፣ ጃኮብ ራምሴ ፣ ቡካዮ ሳካ እና ኤሚል ስሚዝ ሮው ደግሞ የፒኤፍ ኤ የአመቱ ምርጥ ወጣት እጩዎች ተብለው ተመርጠዋል

 👉🏾 ባየርሙኒክ ለሳዲዮ ማኔ ዝውውር 30 ሚሊዮን ፓወንድ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆኑ ተዘግቧል

ሴኔጋላዊው ተጨዋች ከአንፊልዱ ክለብ ጋር መቀጠል እንደማይፈልግ ማሳወቁን ተከትሎ የጀርመኑ ክለብ በሱ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየቱ የሚታወቅ ሲሆን ለማኔም የ 3 አመት ውል ለማቅረብ ተሰናድቷል

 👉🏾 አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ለተጨማሪ አመታት በላዚዮ የሚያቆያቸውን አዲስ ውል ለመፈረም መቃረባቸው ተጠቁሟል

የቀድሞው የቼልሲና የናፖሊ አለቃ በጣሊያኑ ክለብ እስከ 2025 የሚያቆያቸውን ውል የሚፈርሙ ሲሆን በአመትም 3.5 ሚሊዮን ዮሮ እንደሚከፈላቸው በዘገባው ተካቷል!🤯

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New