News

አዲስ ነገር – አዲሱ ሹመት

አምባሳደር ማይክል ሃመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ።
የቀድሞው የቀጠናው ልዩ መልዕከተኛ ሆነው ያገለግሉ የነበሩት ዴቪድ ሳተርፊልድ በቦታው ላይ ለ6 ወራት ያህል ካገለገሉ በኋላ ነው አሜሪካ ዳግም ማይክል ሀመርን ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመችው ።
አሁን የተሾሙት አምባሳደር ማይክል ሀመር ከዚህ ቀደም የቺሊና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አምባሳደርና የአሜሪካ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እንዲሁም በውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትና በነጩ ቤተመንግስት ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነቶች ያገለገሉ መሆናቸውም ተገልጿል።
በተጨማሪም በህግ የሁለተኛ ዲግሪ አላቸው የተባለ ሲሆን ስፓኒሽ፣ ፈረንሳይኛና የአይስላንድ ቋንቋዎችን አቀላጠፈው እንደሚናገሩም ተነግሮላቸዋል፡፡
የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕከተኛ በመሆን ከሰሩት መሃል ጄፍሪ ፊልትማን እንዲሁም ዴቪድ ሳተርፊልድ የሚጠቀሱ ሲሆን አዲሱ አምባሳደር ማይክል ሃመር በቀጠናው ያለውን ትኩሳት ያረግባሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New