አዲስ ነገር – የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር

በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ችግኝ መዘጋጀቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ በ2013 ዓም በተከናወነው የአረጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተተክለዋል ከተባሉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ችግኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ጸድቀዋል ብሏል።
ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት አጠቃላይ ለመትከል ከታቀደው 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ችግኝ መካከል 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን የደን፣ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን የጥምር ደን ችግኝ፣ ከ 5 መቶ ሚሊዮን በላይ የፍራፍሬና ሌሎች መሰል ችግኞች መዘጋጀታቸውንና ለእነሱም የሚሆን ተስማሚ ስፍራ መለየቱን ሚኒስትሩ አስታውቋል።
በተጨማሪም የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለማከናወን ትንሽ ጊዜ ብቻ ቀርቶታል የተባለ ሲሆን ለችግኞቹ የሚሆንም የጉድጓድ ቁፏሮ መከናወኑም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በይፋዊ ማህበራዊ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New