አዲስ ነገር – የአደጋ ስጋት ዌብ ፖርታል
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃዎችን በተደራጀ ሁኔታ ለሚመለከታቸው አካላት አደርስበታለሁ ያለውን ዌብ ፖርታልና ዲጂታል ላይብረሪን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ይህ የመረጃ ማሰራጫ መንገድ የተቋሙን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት የማሳወቅ ስራ የሚሰራበት የመከላከያ መንገድ እንደሚሆንም ተነግሯል።
ከዚህ በተጨማሪ ፖርታሉ የአደጋ ስጋት ማሳያ ካርታዎችን እንዲሁም ከኮሚሽኑ ጋር የተያያዙ ፖሊሲዎችን ጨምሮ የጥናት ውጤቶችና ሪፖርቶችን ብሎም የአየር ጠባይ ትንበያን ጭምር ማካተቱ የተነገረ ሲሆን መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሀን፣ ለአጋር አካላትና ለህዝቡ እንዲደርሱ የሚደረግበት አማራጭ መንገድም ይሆናል ተብሏል፡፡
ይህ ዌብ ፖርታል ትክክለኛ መረጃዎችን በወቅቱ በማሰራጨት የተዛቡ መረጃዎችን የመከላከል አቅም እንደሚፈጥር የተነገረ ሲሆን ዌብ ፖርታሉ በቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ ስለመሰራቱ ተነግሯል።
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:00 ሰዓት እስከ 7:30 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New