አዲስ ነገር – የወታደራዊ ትብብርና የብድር ስምምነቶች

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በኢትዮጵያና ቱርክ መንግስታት መካከል የተደረጉትን የወታደራዊ ማዕቀፍና የወታደራዊ ፋይናንስ ትብብር ስምምነቶች እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ጋር የተደረሰውን የብድር ስምምነት አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ስምምነቶቹን ያጸደቀው ትላንት 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ሲሆን የወታደራዊ ትብብር ስምምነቶቹ አገራቱ የመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ መረጃ ልውውጥና የሳይበር ጥቃትን መከላከልን ጨምሮ በተያያዥ መስኮች አብረው እንዲሰሩ ያስችላል ተብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈ የባለሙያዎች፣ የቁሳቁስ፣ የመረጃና የልምድ ልውውጥ እንዲሁም የጋራ ወታደራዊ ልምምድም በስምምነቶቹ ተካተዋል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ግብአቶችን፣ የሎጅስቲክ አቅርቦትንና ድጋፎችን እንድታገኝ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ጋር የተደረገው የብድር ስምምነት ለገጠር ፋይናንስ ስርዓት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ማስፈጸሚያ የሚውል መሆኑ ሲገለጽ ስምምነቱ በ3 ተቃውሞ በ8 ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁም ታውቋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New