News

አዲስ ነገር – የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ

ሰላምንና አንድነትን ለማረጋገጥ ጉልበትን እንደ አማራጭ መውሰድ በማቆም ችግሮችን በውይይትና በድርድር ለመፍታት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ጥሪውን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሲሆኑ የ2014ን የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በከፈቱበት ወቅት ሰላም ለሃይማኖት መጠበቅና ለህዝብ ደኅንነት ዋጋው ትልቅ ነው ብለዋል፡፡
ይሁንና ሰላም ሳይጠበቅ ቀርቶ በተከሰቱ ግጭቶች ህዝቡ መንገላታቱን ጠቁመው አሁን ላይ የሚታየው አካሄድ ራስን የማስበለጥና የሌላውን የማሳነስ በመሆኑ ይህን ተግባር በማረም በመተሳሰብ፣ በትህትናና በፍቅር ወደ አንድነት መመለስ እንደሚገባ አስረድተዋል።
ህዝቡን ወደ እርቅና ወደ ይቅርታ ማምጣት የሃይማኖት አባቶች ቀዳሚ ተግባር መሆኑን በመጠቆምም በዚህ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ምልአተ ጉባዔው ራሱን ከማናቸውም አደረጃጀቶች ነጻ በማድረግ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላም መሥራትና መጣር ይጠበቅበታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዜናው የሰላማዊት ሽፈራው ነው።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New