Sports

EBS SPORT – ኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ጨዋታ የፊታችን አርብ የናይጄሪያ አቻውን በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም ይገጥማሉ፡፡ ለታላቁ የታዳጊዎች ውድድር ለማለፍ 180 ደቂቃዎች የሚቀራቸው ታዳጊዎቹም ለዚህ ጨዋታ ዝግጅት ላለፉት ሳምንታት በወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

3 ዙሮችን ባለፈው ውድድር ኡጋንዳ እና ደቡብ አፍሪካን በድምር ውጤት አሸንፈው ወደ መጨረሻው ምዕራፍ የተሻገሩት ታዳጊዎቹ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ ቡድኑ ጥሩ የሚባል ልምድ እንዳገኘበት በተገለፀው ጨዋታም 1-1 በሆነ  አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ቡድኑ ከሳምንቱ መጀመሪያ ቀን  አንስቶ የልምምድ ቦታውን ከወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ በመቀየር ጨዋታውን ወደሚያደርግበት አበበ ቢቂላ ስቴዲየም መቀየሩም ተነግሯል፡፡

የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ላይ የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴቶች ቡድን  ከዚህ ቀደም ከነበረው መንገድ በውጤት በተሻሉበት ሂደትም 4 ጨዋታዎችን አድርገው 6 ግቦችን ተጋጣሚያቸው መረብ  ላይ ማሳረፍ ችለዋል፡፡ በ2018 በተመሳሳይ የመድረኩ የማጣሪያ ከናይጄሪያ አቻቸው ጋር በነበራቸው ጨዋታም ታዳጊዎቹ ሁለቱንም ጨዋታዎች በአቻ ውጤት መፈፀማቸው ደግሞ የቅርብ ጊዚ ትውስታ ነው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New