አዲስ ነገር – የዋና ኦዲተር ሹመት

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባው ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የቀረቡለትን ሹመቶች አጽድቋል፡፡
በዚህም ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ የፌደራል ዋና ኦዲትር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ሆነው ሲሾሙ፤ አቶ አበራ ታደለ የፌደራል ዋና ኦዲትር ምክትል ዋና ኦዲትር ሆነው በሙሉ ድምጽ ተሹመዋል፡፡
ተሿሚዎቹም በህዝብ አንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ በነገራችን ላይ ተመልካቾቻችን ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 12ኛና መደበኛ ስብሰባው ከሹመት ጉዳይ በተጨማሪ ሌላ አንድ አጀንዳ ላይም ተወያይቷል፡፡
በዚህም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርን የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸም አድምጦ የገመገመ ሲሆን በመድረኩ ላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ የመሬት ወረራ፣ የመንግስት ህንጻዎች ግንባታ እንዲሁም በርካታ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ እኛም እነዚህኑ ጉዳዮች አካተን በምሽት የአዲስ ነገር ዜና መጽሔታችን በዝርዝር የምንነግራችሁ ይሆናል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New