News

አዲስ ነገር – የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሀመድ በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም ሞቃዲሾ ገብተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ውስጥ ተካተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲሱ ተሿሚ ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሀመድ ጋርና በበዓለ ሲመቱ ላይ ከሚታደሙ ከሌሎች አገራት መሪዎች ጋርም የሁለትሽ ምክክር እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New