News

አዲስ ነገር – የምርጫ አስፈጻሚዎች የምስክር ወረቀት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ የምርጫ አስፈጻሚዎች የምስክር ወረቀት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
ቦርዱ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ ሠራተኞች ማለትም የዞን አስተባባሪዎች፣ የምርጫ ክልል ኃላፊዎች፣ የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዳታ ኢንኮደሮችና የአይ.ሲ.ቲ ባለሞያዎች ለነበራቸው ተሣትፎ ያመሰገነ ሲሆን የምስክር ወረቀት በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ፖርታል ማዘጋጀቱንም ገልጿል።
በዚህም የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የምስክር ወረቀት መጠየቂያ ፖርታሉ ላይ የሚገኙትን መረጃዎች በማስገባት የምስክር ወረቀታቸውን መውስድ እንደሚችሉ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ባወጣው ጽሁፍ አመልክቷል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New