News

አዲስ ነገር – የሰብዓዊ እርዳታ

ወደ ትግራይ አማራና አፋር ክልሎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቱን በመደበኛነት እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን ተግባር የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አድንቋል።

ባለፉት ሰባት ቀናት አንድ ሺህ 100 ተሽከርካሪዎች የሰብዓዊ እርዳታ ይዘው ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸው የሚበረታታ ተግባር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶኒዮ ብሊንከን ያስታወቁ ሲሆን እርዳታው በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጎዱ ሰዎችን ለማከም የሚያስፈልጉ ግብዓቶች፣ የህክምና አቅርቦቶች እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን እንዳካተተ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለሶስቱ ክልሎች እየተደረገ ያለውን ወጥ የሰብዓዊ ድጋፍ ያበረታቱት ሚኒስትሩ መንግስት እያደረገ ካለው በተጨማሪ ሁሉም ወገኖች ግጭትን በዘላቂነት ለማቆም ጥረት እንዲያደርጉ በመግለጫቸው መክረዋል፡፡
በሌላ በኩል በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት በዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የፈጸሙ አካላትም ተጠያቂ እንዲሆኑ ሀገራቸው እንደምትሻ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New