አዲስ ነገር – የጎርፍ አደጋ ስጋት

በቀሪው የክረምት ወራት በሚኖረው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሳቢያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል።የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሃገሪቱ በቀጣይ ወራቶች በሚኖረው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሳቢያ የተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ወንዞች ከመጠን በላይ በመሙላት በአካባቢው ላይ በሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ አደጋ የሚያስከትሉ በመሆናቸው አደጋው ከመድረሱ በፊት መቆጣጠር የሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየሰራሁ እገኛለሁም ብሏል።ይህን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ይመለከታቸዋል ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆንም ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት እንዲያስችለው የውይይት መድረክም ማካሄዱንም ሰምተናል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New